ኢየሱስ ያለህበት ሰላሜ ያለበት(4*) አንተ የዋልክበት ደስታዬ ያለበት(2*) አንተ የከበርክበት ስኬቴ ያለበት(2*) የተጠራህበት መድሃኒቴ ያለበት(2*) ነፍሴ የምትወድህ ሆይ ሁሉም ይቅርና አንተ ዋል ከቤቴ ነፍሴ የምትናፍቅህ ሆይ ሌላው ይቅርና ብቻ ዋል ከቤቴ የምፈልገው አንተን ነው ሁሌ የምመኘው አንተን ነው እኔ የሚመቸኝ ቤትህ ነው የምታስፈልገኝ አንተ ነህ ፈልጌ አይደለም ከእጅህ አንድ ጉርሻ እንድንዘልቅ እንጂ እስከ መጨረሻ ከአንተ ጋር አኑረኝ ይሄ ነው ፀሎቴ ቢከፋኝ ቢደላኝ እግርህ ስር ነው ቤቴ ነፍሴ የምትወድህ የምፈልገው በመንፈስህ ልስከር ሙላኝ በየእለቱ አንተም አልነጠል ላፍቅርህ በብርቱ በድንግዝግዝ አልኑር አይኖቼን አብራልኝ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን አስተምረኝ ነፍሴ የምትወድህ በምትሰራበት ቀን እንዳልሆን እንግዳ በሩቁ አጨብጫቢ ታዛቢ እንደ ባዳ ከእግርህ ስር ቁጭ ብዬ ልማርህ እሻለሁ የልብህን ሃሳብ ፈቃድህን እንዳውቀው የምፈልገው