Song Lyrics

ባለውለታዬ

ወረቀት ብዕሬን አገናኘሁኝ ስለጌታ ውለታ መጻፍ አሰኘኝ የትኛውን ጽፌ የቱን ልተወው የምለውን ባጣ እንዲህ ልበለው ልበለው ባለውለታዬ ነው ጌታዬ (4x) ውለታ አለብኝ የማልመልሰው የ እግዚአብሔር ልጅ ለእኔ የሰራው ስለ ኢየሱስ ሰፊ ጊዜ ያሻኛል እንኳን ቀኑ ዘላለም ያንሰኛል ታሪክ የሌለውን ባለታሪክ ጠላት የሆንኩት ወዳጅ አረክ አሳዳጅ የሆንኩትን ነካኽኝና በቅዱሳኑ ፊት አቆምከኝና ዘምር አልከኝ (4x) በስንኝ ቋጠሮ ችዪ ላልሰንቅ ጠልቄ ባስብም አቅሜ እስኪያልቅ አወይ በትንሿ በዚች ወረቀት ጭሬ አልጨርሰው የሱን ሰጪነት ለጋስነት መካኒቱ ሰባት ወለደች ሳራም በእርጅና ጸነሰች ሙሴን በጥበብ አሳደገ ምስኪኑን ዳዊት ንጉሥ አደረገ እንደዚህ ነው የኢየሱስ ስራ አይጨረስ ሁሌም ቢወራ እኔም አለኝ የምለው አግኝቶኛል ውለታው ባለውለታዬ ነው ጌታዬ (4x) ውለታ አለብኝ የማልመልሰው የእግዛብሄር ልጅ ለእኔ የሰራው ስለ ኢየሱስ ሰፊ ጊዜ ያሻኛል እንኳን ቀኑ ዘላለም ያንሰኛል ብዙ ነው የሱ ውለታ ሳስበው ጥዋት እና ማታ ግርም ይለኛል ድንቅ ይለኛል ቃላት ያጥረኛል በምን ቋንቋ ነው በምን አንደበት የምገልጸው የሱን በጐነት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection