Song Lyrics

የውሃ በረሐ

ብዙ ፍጥረት ያለው ባህር ውቅያኖሱ ለየብስ እሩብ ሰጥቶ ቀሪውን መልበሱ ላጥፋ ካለ አጥፊ ጡንቻ ያለው ፈርጣማ ከአንዱ ጌታ በቀር ማንንም አይሰማ ጥም አርኪ ይመስላል ግን ለጠማው ደሃ ውስጡ ስለሌለ ለመጠጥ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ ሰነፍ መርከበኛ ውቅያኖሱ ዳር ሚጠጣውን ሳይዝ መጓዝ ቢጀመር ውሃ መሀል ደርሶ ውሃ ይጠማዋል ውሃ በረሐ ላይ በውሃ ጥም ይሞታል አንድ ጉድጓድ አለች በጣም ትንሽዬ ሕፃን ነህ አዋቂ ጨዋ ነህ ዱርዬ ሳትል ሳታዳላ ሁሉን ታጠጣለች ይሄን ንፁህ ውሃን ታመነጨዋለች ጠቢቡ ገበሬ እሷ ዳር ይዘራል ስሩ ምንጯን ነክቶ ማን ደርቆ ይቀራል ጌታ ኢየሱስን በእምነቱ የነካ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ ረካ ስንት ምስኪን አለ ሳይተኛ ሚያነጋ ነፍሱ ምትገረፍ በጥማት አለንጋ እግዚአብሔር ነፍሱን ነይ ላርካሽ ቢላት የእግዚአብሔርን ሳይሆን ለነፍሱ ሆዱን ሰማላት ጌታ በሌለበት በዛ ባዶ ቦታ ምኑንም ቢከቱ አይሰጥም እርካታ ሰማይና ምድር በአንዴ ተጠቅልሎ የኢየሱስን ቦታ አይሞላውም ችሎ የተከበበ በማይጠጣ በአለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ በጀልባው እንደጠፋ ውቅያኖስ ላይ ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ? ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ ኑሮ ማለት ሐሩር ከሌለው ጌታ ዳግም አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection