አዝ፦ መዳኛ ነህ መዳኛ (2x) ለተረሳው ሰው ጓደኛ መዳኛ ነህ መዳኛ አባቴ ነህ አባቴ (2x) አሳደከኝ ከልጅነቴ አባቴ ነህ አባቴ (2x) ህልመኛው ተሽጦ ለግብፃዊ ቤት አገልጋይ እንዲሆን ለረጅም ዓመት (2x) ሲመላለስ ሳለ በታማኝነት በሀሰት ወንጅለው ከወይኒ ጣሉት (2x) ለመልካም ሆነለት አንተን በማክበሩ ህልሙ እውን ሆነ ወጣ በመምበሩ (2x) ሰው ሳያይ በጓዳ እግዚአብሔርን ፈሪ መሆኑ አይቀርም ተፅዕኖ ፈጣሪ (2x) የተጣለን ምታነሳ ለምስኪኑ ምትሳሳ የታሰረን የምትፈታ የደህንነት ጌታ (2x) አዝ፦ መዳኛ ነህ መዳኛ (2x) ለተረሳው ሰው ጓደኛ መዳኛ ነህ መዳኛ አባቴ ነህ አባቴ (2x) አሳደከኝ ከልጅነቴ አባቴ ነህ አባቴ (2x) መከራው ስቃዩ ሲያልፍ በሕይወቴ ከጐኔ አልተለየህ ኢየሱስ ረዳቴ ኢየሱስ አባቴ እንዳያልፍ አለፈ ያ ሁሉ መከራ ሃሩር ተሻገርኩኝ ከጌታዬ ጋራ ከኢየሱሴ ጋራ የበረሃው ፀሐይ እንዳያቃጥለኝ ደመናን አዞልኝ ጥላ አደረገልኝ (2x) እባብ እና ጊንጡ ነድፎ እንዳያስቀረኝ ከፊቴ እየወጣ እረጋገጠልኝ (2x) አዝ፦ መዳኛ ነህ መዳኛ (2x) ለተረሳው ሰው ጓደኛ መዳኛ ነህ መዳኛ አባቴ ነህ አባቴ (2x) አሳደከኝ ከልጅነቴ አባቴ ነህ አባቴ (2x)