ተጭኖብኝ የማልችለውን የሞት ፍርሀት አርጎኝ ምስኪን መች አገዝኝ የእኔነት ካባዬ አልቆ ነበር የመኖር ተስፋዬ ግን አንድ ቀን ወንጌል ሰማሁኝ ይታደጋል ያድናል ሲሉኝ በቅንነት እጄን አነሳሁኝ የዛች ለት ጌታን አገኘሁኝ አዲስ ነገር የዛች ለት ሆነ (2x) በመንፈሴ ሰላም ሰፈነ (2x) አፈሰሰው በልቤ ደስታ (2x) መንፈስ ቅዱስ የሰላም ጌታ (2x) በአገር በሰፈሩ እታማ ጀመረ የእናት እና የአባቱን ሃይማኖት ቀየረ ይህን ያንን ብለው በእኔ ላይ ተነሱ እኔ የቀመስኩትን ምነው በቀመሱ ኢየሱስ ብቸኛ አማራጭ የሌለው ወደ ሰማይ መግብያ ብቸኛ መንገድ ነው ያዳነኝ ኢየሱስ ነው የሞተልኝ ኢየሱስ ነው በመስቀል ላይ ኢየሱስ ነው የተወጋልኝ ኢየሱስ ነው ዋጋ ከፍሎ ኢየሱስ ነው በደም ገዛኝ ኢየሱስ ነው ከጻድቃን ጋር ኢየሱስ ነው የቀላቀለኝ ኢየሱስ ነው መዘበቻ አርጓት ነፍሴን ሰይጣን ክፉ አይራራ አያዝን ከሱ ለማምለጥ ብዙ ጣርኩኝ ግን አልቻልኩኝ በዚህ ሁኔታ ወንጌል ሰማሁኝ ኢየሱስን ተገናኘሁኝ ሰው መሆኔን የወደድኩት ያየሁት ለት የልጅነትን ሥልጣንን ሰጠኝ ሥልጣን ያሳደደኝን አሳደድኩኝ አሳደድኩኝ የበቀል ቅባት እራሴን ቀባኝ እራሴን ቀባኝ ያስጨነቀኝን አስጨነኩኝ አስጨነኩኝ እናንተ ደካሞች ሸክማቹህ ከባድ ወደ እኔ ኑ ያለ ይሄ ሰውን ወዳጅ ያሳረፈኝ ኢየሱስ ነው ሰው ያደረገኝ ኢየሱስ ነው ያከበረኝ ኢየሱስ ነው ያዘመረኝ ኢየሱስ ነው ዋጋ ከፍሎ ኢየሱስ ነው በደም ገዛኝ ኢየሱስ ነው ከጻድቃን ጋር ኢየሱስ ነው የቀላቀለኝ ኢየሱስ ነው