Song Lyrics

ሁሉን ቀድሜዋለሁ

የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ ጥበበኛዋ ሴት ቀዝቃዛውን ክረምት ሩቅ አይታ ልብሷን ሰፋች መከራውን ቀደመች እኔም እንደ እሷ ሁሉን ቀድምያለሁ በኢየሱስ ተደስቻለሁ (2x) ሃዘንን ቀድሜዋለው ጭንቀትን ቀድሜዋለው ተድላን ቀድሜዋለው ስኬትን ቀድሜዋለው የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ የተቀደመ ነው የቀረው ዘመኔ የዘላለም ደስታ ኢየሱስ ሆኖኝ ለእኔ ቀድሜ ተደስቻለው (2x) በኢየሱስ ተደስቻለው (2x) እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (3x) ይፍለቀለቃል ከውስጤ አይቋረጥም ሰላሜ (3x) ይፍለቀለቃል ከውስጤ የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (2x) ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ ደስታ እና ሃዘኔ እኩያ ነበሩ በልኬት ቁመና የሚፎካከሩ ኢየሱስ ግን የሰጠኝ ደስታ አይስተካከል ከሁኔታ አባቴ የስጠኝ ደስታ አይስተካከል ከሁኔታ እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (3x) ይፍለቀለቃል ከውስጤ እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (3x) ይፍለቀለቃል ከውስጤ የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ አንተ ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection