Song Lyrics

አቤት ደግነት

እውነትነቱን በመስቀል ላይ መቶ አለቃው ጌታዬን ቢያይ ተንበረከከ ሰገደለት ነካው የጌታ ቅንነት እንኳን አሁን ከፍ ከፍ ብሎ አሸንፎአል ተንጠልጥሎ ሳያስፈራራ ሰው አንበርካኪ እንደእርሱ የለም ፍቅር ሰባኪ አቤት ደግነት ቸርነቱ ለሰው ያሳየው ምህረቱ (6x) ፍቅር ምህረቱን የቀመሱቱ ውበቱን ያዩ ሐዋሪያቱ ስለእርሱ ኖረው መረጡ ሞት ለፍቅሩ ሆኑ ሰማዕታት ተነክተው በምህረቱ ተነክተው በቸርነቱ ነክቶአቸው ገርነቱ ነክቶአቸው የዋህነቱ የቱ ጀግና ነው እጁን ያልሰጠ የሱስን አይቶ ያልደነገጠ ልከተልህ ያላለ ማነው የኢየሱስ ፍቅር አሸናፊ ነው ከጫፍ ጫፍ ስንቱን ማረከ በፍቅሩ አንበረከከ ምን ዓይነት ፍቅር ነው እንጃ ወደደንው/ሰገድንያለጠመንጃ (2x) አቤትትህትናአይቅንነት ሰውንያስተማረኖሮበሕይወት የሚሸጠውንእግር ያጠበ ሩህሩህ ነው ጌታፍቅርያነገበ ይህንን ጌታ የምትወዱት አስቲ ከእኔ ጋር ኢየሱስን እንዲህ በሉት (2x) እንዳንተ ያለ እንዳንተ ያለ እንዳንተ ያለ ኧረ ማን አለ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection