በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ ይበላል ትዕግስቱ ያላለቀ ጌታውን የጠበቀ ሰው ስፍራዬን አልለቅም ያለው እሱ ሰው ከበረ ጌታን ያከበረ ስምዖን ትጉህ እና ጻድቅ ሰው ነበረ አያለሁ ቅዱሱን እያለ የኖረ ሲጠብቅ ቆይቶ ህፃኑን ሲያየው እጆቹን አንስቶ እንደዚህ አለው ለህዝቦች ሁሉ መድሃኒት የሆነውን እርሱን ስላየሁት መኖር አልሻም ውሰደኝ በቃ በፅድቅ የኖርኩት እሱን ጥበቃ (ጌታን ጥበቃ) ለኔ ስኬት (3) ልጁን ማየት ለኔ ከፍታ (3) ፊትህ ነው ጌታ ያርስ የለ ወይ በበጋ ልቡን ጥሎ ገበሬው አምኖ ይዘንባል ብሎ በደረቅ አምኖ ያረሰ በክረምት እርሻው ረሰረሰ እኔም እጠብቅሃለሁ መውደዴን በዚህ አሳይሃለሁ አንድ ቀን አለም እያየ ልትወስደኝ ትመጣልኛለህ እስክትመጣ እስክትመለስ እጠብቅሃለሁ ውዴ ኢየሱስ ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ ይበላል ትዕግስቱ ያላለቀ ጌታውን የጠበቀ ሰው ስፍራዬን አልለቅም ያለው እሱ ሰው ከበረ ጌታን ያከበረ ፍፃሜው ክብር ነው አንተን መጠበቄ መብራቴን አብርቼ ወገቤን ታጥቄ እጠብቅሃለሁ እስክትመለስ ሙሽራውን አዳኜ ጌታዬ ኢየሱስ ፊትህን እንዳይ ተርቤ የለ ወይ (እርቦኝ የለ ወይ) ለጥቂቶች መዳን ብትዘገይ ጨመረብኝ ፍቅርህ በየእለቱ ተናፍቀሃል ኢየሱስ የናዝሬቱ እስክትመጣ እስክትመለስ እጠብቅሃለሁ ውዴ ኢየሱስ ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ