ለካ ይታለፋል ማይታለው ከልኩ አያልፍም የሰው ፈተናው የምጠፋ መስሎኝ ፈራች እንጂ ነፍሴ ለካ ያስጨነቅከኝ ለጥቅሜ ለራሴ በእሳት እያለፍኩ ስፈተን ወርቅ አደረገው ህይወቴን ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር እቃ ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ ልቤን አጀገነው ቅዱሱ መንፈስ ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ መቼ መሰለኝ የምሰራ ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ (2) ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ (2) ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ ለመልካም ሆነልኝ ያስጨነቅከኝ ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ ለበጎ ሆነልኝ ያስጨነቅከኝ በመከራ ውስጥ መታዘዝን ተማረ በስጋው ወራት አንተን አከበረ እኛ ዳንን እንጂ በእርሱ መከራ ህይወታችን ጣፍጧል በጠጣው መራራ እርሱ ሃያል ሳለ ምስኪን መሰለ ከአመፀኞች ጋር ተሰቀለ በጌታ መከራ ስንቶች ዳኑ አቀረባቸው ወደ ዙፋኑ ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር እቃ ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ ልቤን አጀገነው የጌታ መንፈስ ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ መቼ መሰለኝ የምሰራ ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ (2) ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ (2) ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ ለመልካም ሆነልኝ ያስጨነቅከኝ ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ ለበጎ ሆነልኝ ያስጨነቅከኝ