Song Lyrics

አሜን

አሜን አሜን (16) ወንጌል ሲነገረኝ አትንገሩኝ ባይ ጠንካራ ነበረ እንደ ድጋይ ግን አንድ ቀን ጭንቀት ወደ ህይወቴ መጣ እውቀቴ መሰለኝ ምንም አላመጣ ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ ልሞክረው ብዬ በስብከት ሞኝነት ይሁን አሜን ብዬ አይቼ የማላውቀው የደስታ ካባ ህይወቴ ለበሰ ኢየሱስ ሲገባ ዛሬማ እሞትለታለሁ ሂድ ቢለኝ ወዴት እሄዳለሁ እሱ ነው የመጨረሻዬ አሜን ያልኩት ኢየሱስ ጌታዬ አስገባሁት (አሜን) ልቤን ከፍቼ (አሜን) ይኸው አለሁኝ (አሜን) ድኜ ቀርቼ (አሜን) ያስገባሁት (አሜን) አሜን ብዬ (አሜን) መድሃኒት ሆነኝ (አሜን) ኢየሱስዬ (አሜን) ኢየሱስዬ (ውድዬ) (4) አሜን አሜን (16) እንኳንስ ሊያቀርበኝ ሊገባ ከቤቴ መጥራት ማይገባኝ ስሙን በአንደበቴ ጌታ ግን ደግ ነው ምህረት የለበሰ ለጠፋሁት ልጁ ፍቅርን ደገሰ ፍርግ ነበረብኝ በሞት የሚያስቀጣ የገዛ በደሌ ያመጣብኝ ጣጣ ጌታ ግን ከፈለው የሃጥያቴን እዳ አሜን በማለቴ ነውሬን አፀዳ በኢየሱስ ህይወት አግኝቻለሁ ልለየው እንዴት እችላለሁ እስካይችል ይኼ ትከሻዬ አይሏል ፍቅሩ በላዬ አስገባሁት (አሜን) ልቤን ከፍቼ (አሜን) ይኸው አለሁኝ (አሜን) ድኜ ቀርቼ (አሜን) ያስገባሁት (አሜን) አሜን ብዬ (አሜን) መድሃኒት ሆነኝ (አሜን) ኢየሱስዬ (አሜን) ኢየሱስዬ (ውድዬ) (4) አሜን አሜን (16) ከሰማይ ወደ አሜን አሜን ደግሞ አሜን አሜን ከሙታን ተነሳ አሜን አሜን በክብር አረገ አሜን አሜን ልክ እንደመብረቅ አሜን አሜን ከላዬ አበራ አሜን አሜን ዳግም ይመለሳል አሜን አሜን ከቅዱሳን ጋር አሜን አሜን ስምን ያተረፉ በየዘመናቸው ተከታዮቿቸው ሲሞቱ ረሷቸው ሁለት ሺ አመት ታሪክ ያልሸፈነው ሰንጥቆ የመጣ የኢየሱሴ ስም ነው ይሄን ስሰማ አሜን በማለቴ ሰመረ ብርሃን በራ ቤቴ አሜን በማለቴ (3) ሰመረ ህይወቴ አሜን ያልኩት ጌታ (3) እስራቴን ፈታ አሜን አሜን (15)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection