የሞተን በቃሉ የሚያነሳ ደግሞም የሚፈውስ ሳይታይ ጠባሳ ምስክር ለሚሻ እኔ አለሁ በስሙ አምኜ ተፈውሻለሁ እንኳን ፊቱ ያለሁቱ ዳኑ ከጀርባ የነኩቱ ኢየሱስ ብሎ የተጣራ በልቷል ፈውስን እንደ እንጀራ እንኳን ስሙን ያመንኩቱ ዳኑ ከጀርባ የነኩቱ ኢየሱስ ብሎ የተጣራ በልቷል ፈውስን እንደ እንጀራ ፈውስን እንደ እንጀራ (እንደ እንጀራ) አገር የሚያውቃት ከቤተ መቅደስ ስትመላለስ ለፈውሷ ሳይሆን አምላኳን ወድዳ ቀድማ የምትደርስ ያሸማቀቃት ያስጎበጣት ጀርባዋ ላይ ይዛ ስትገባ ለካ ቀድሟታል ቅኖች የሚያይ ቢዳስሳት ጌታዋ ተፈወሰ ጀርባዋ ወደቀላት ቀንበሩ ስለመጣ መምህሩ አዳኝ መጥቷል መምህሩ ፍቅር መጥቷል መምህሩ ንጉስ መጥቷል መምህሩ ፈዋሽ መጥቷል መምህሩ ደከመኝ ሳትል ተመላለሰች ህመሟን ይዛ እቤቱ መጣች ልክ እንደ ልማዷ ከምኩራብ ስትደርስ የዛንለት ሰባኪው መምህሩ ኢየሱስ ቢዳስሳት ጌታዋ ተፈወሰ ጀርባዋ ወደቀላት ቀንበሩ ስለመጣ መምህሩ አዳኝ መጥቷል መምህሩ ፈዋሽ መጥቷል መምህሩ ርህሩህ መጥቷል መምህሩ ፍቅር መጥቷል መምህሩ ፍቅር መጥቷል (መምህሩ) ልጅቷ ሞታለች አታድክም መምህሩን ለወላጅ አባቷ ብለው አረዱት መርዶውን አትፍራ ብቻ እመን ሰምቶ አለው ጌታ እቤታቸው ሄደ በዛ ለቅሶ ጫጫታ ተኛች እንጂ መች ሞተች ቢላት ሳቁ ለቀስትውኞች ጌታ ወደ ውስጥ ገባ እና ተነሽ አንቺ ብላቴና በድኗ ልጅ ተነሳች የጌታን ድምፅ ሰማች ሙታን አቤት የሚሉት ኢየሱስ የአለም መድሃኒት ሙታን አቤት (መምህሩ) የሚሉት ኢየሱስ የአለም (መምህሩ) መድሃኒት (2) ኢየሱስ የኔ (መምህሩ) መድሃኒት እንኳን ፊቱ የጀርባውም ቀሚስ አይተን የለም ወይ የነካው ሲፈወስ አልዳነችም ወይ ያቺ ምስኪን በእምነት ብትነካው ቀሚሱን እንኳንስ ፊቱ ጀርባው መድሃኒት አምኖ ለነካው የሚሰጥ ህይወት የሚያገፋፋው አላማኝ መች ታጣ በእምነት ለነካች ከጀርባው ሃይል ወጣ ፈውስን እንደ እንጀራ (እንደ እንጀራ) እንኳን ስሙን ያመንኩቱ ዳኑ ከጀርባ የነኩቱ ኢየሱስ ብሎ የተጣራ በልቷል ፈውስን እንደ እንጀራ ፈውስን እንደ እንጀራ (እንደ እንጀራ) ይሄን ወንጌል ያልሰማ እንዲሰማ አውጃለሁ ከገጠር ከተማ እንደሚያድን እንደሚታደግ እሰብካለሁ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ያድናል የምለው እኔ አድኖኝ ስላየሁ ባይኔ ያድናል እኔ ያልኩት አድኖኝ ስላየሁት ያድናል (8)