Song Lyrics

አቤት ምህረትህ

አቤት ምህረትህ እንዴት ታላቅ ነው (2) መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው ያንተ ምህረትህ ከማን ጋር ይስተያይ ከፈጠርከው ፍጥረት ከምድር ወይ ሰማይ የሚስተካከልህ ማን አለ በውኑ አባቴ ምህረትህ ያክላል አንተኑ መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው ሳትታሰብ ጠላት እንጅ ቀርቶ ሳምሶም ወደቀ ከመስመር ወጥቶ ግን ምህረትህ ታምኖ መቼ አፈረ የራሱ ፀጉር ማደግ ጀመረ በህይወት ከሰራው በሞቱ ባሰ ለዛ ኪዳን ሰው ምህረት ደረሰ አንድ እድል ብቻ ባይለምንህ ይኖር ነበር በቸርነትህ እንዴት (3) ታላቅ ነው እንዴት (3) ታላቅ ነው ኧረ እንዴት እንዴት (3) ታላቅ ነው እንዴት (3) ታላቅ ነው ያንተ ምህረት አቤት ምህረትህ እንዴት ታላቅ ነው (2) መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው ብትጨምርለት አስራ አምስት አመት ተዝቆ በማያልቅ ከሰፊው ምህረትህ ከኖረበት እድሜ ከምህረትህ ወስዶ አንተን ሳያከብር ጨረሰው በባዶ እኔ ግን ገብቶኛል የቃልህ እውነት ለካ የምዘምረው ባንተ ምህረት መሃሪነትህን እዘምረዋለው በጉልበቴ ሳይሆን በምህረት እኖራው እንዴት (3) ታላቅ ነው እንዴት (3) ታላቅ ነው ኧረ እንዴት እንዴት (3) ታላቅ ነው እንዴት (3) ታላቅ ነው ያንተ ምህረት መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection