Song Lyrics

አለሁ

አለሁ በምህረቱ አለሁ በይቅርታው አለሁ አለሁ ምህረት አግኝቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አለሁ በምህረቱ አለሁ እየማረኝ አለሁ አለሁ ምህረት አግኝቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህሩቱ ገኗል አለሁ ህመምሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ እነሚካኤል እነገብሬል እነሱራፌል እነኪሩቤል በክንፎቻቸው ተከልለውት ፊቱ ሚቆሙለት አምላክ የሚሉት በገራፊዎች ፊት ቆመልኝ እሱ ግን ስለኔ ፈቅር ግድ ቢለው ሊያወጣኝ ከሃጥያት ከኩነኔ ዙፋኑ የነበረው ከሰማይ ዳዊትን የረዳ ተንከታተተልኝ ኢየሱስ ከነዝሬት ይሁዳ ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ ኑሮዬን ኑር አለኝ የኔን ልብስ ለበሰ ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህሩቱ ገኗል አለሁ ህመምሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ ይሁን በምትል ቃል ፍጥረትን የሰራ ጥበብ የሻተውን ጥበብን ያስወራህ አባቶች ሲጠሩት በእሳት የመለሰ እረኛው ዳዊትን ተናግሮ ያነገሰ እንደሚታረድ በግ ዝም አለ ስለኔ ኢየሱስ ፍቅርን የኖረ በተግባር የፍቅር ንጉስ ምድርን ያቆመ በቃሉ ያላንዳች ምሶሶ እሱ ግን ዝም አለ ሞተልኝ የእኔን ውርደት ለብሶ ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ ኑሮዬን ኑር አለኝ የኔን ልብስ ለበሰ ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህሩቱ ገኗል አለሁ ህመምሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አለሁ በምህረቱ አለሁ በይቅርታው አለሁ አለሁ ምህረት አግኝቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አለሁ በምህረቱ አለሁ እየማረኝ አለሁ አለሁ ፍቅሩን ቀምሻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ አለሁ ምህሩቱ ገኗልን አለሁ አለሁ ህመምሜን ወስዷል አለሁ አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ አብ ከላይ ሆኖ ለኔ ራራልኝ አዘነ ሊያድነኝ ሽቶ አንዱ ልጁ ላይ ጨከነ ፍቅር ልሂድ አለ ታዘዘ ለአባቱ ክብሩን ትቶ ወርዶ አዳነኝ በሞቱ ፍቅር እንደ ኢየሱስ የለም (8)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection