ብቻዬን ቁጭ ብዬ አዝኜ በቤቴ በጣም እያመመኝ ይሄው ስብራቴ በድንገት ኢየሱስ ደረሰልኝ ሰባራውን ጠጋኝ እውነተኛ ዳኛ የደካሞች አሳራፊ ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ አዝ:- ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ የፈተና መዓት በላዬ ቢፈስ ፀሎቴም በሙሉ ባይመለስ ዝቅ ዝቅ እላለሁ ሌላ አያምረኝም ቤዛዬን ኢየሱስ በፍፁም አልክድም (2x) አዝ:- ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ ኃጢአተኛ ሳለሁ ሰዎች ሲገፉኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ አይቶ ራራልኝ እንደ ኃጢአቴ ያልፈረደብኝ የእግዚአብሔር ልጅ እርሱ ለእኔ አዘነልኝ አዝ:- ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ የደካሞች አሳራፊ ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ አዝ:- ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ