Song Lyrics

ፀጋው ነው

Bereket Tesfaye
Like Kahine
አዝ:- ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (2x) ሁልጊዜ ችኩል ነው ሲያዩት ደፋር መሳይ ዶሮ ሳይጮህ በፊት ሶስት ጊዜ ክህዶታል በሰው አይን ቢሆን ይህ ሰው ከሀዲ ነው የፀጋው ጉልበት ግን ዳግም ሰው አረገው አዝ:- ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (2x) ቢሆንማ ኑሮ በክብር በዝና በገንዘብም ብዛት ብዙ ብልጥግና እንዴት እሆን ነበር እርቆኝ መዳኔ ግን እንዲያው ወደደኝ አሰበኝ መድህኔ እንደ ሰው አይደለም ጌታዬ ልዩ ነው የተረሳውን ሰው እንዲህ ሚያስታውሰው አዝ:- ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (2x) በማይመስል ነገር መስራት የሚችል የአለምንም ጥበብ በኔ ሚያሳፍር ልጁንም ገለጠው በእኔው ሁኔታ እኔን ውዳቂውን አከበረ ጌታ አዝ:- ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (2x) በራሴ አልቆምኩም ሚስጥሩ ገብቶኛል ጸጋን አትረፍርፎ ኢየሱስ ሰጥቶኛል ከቶ ዝም አልልም አዜምለታለሁ ላከበረኝ ጌታ ክብር እሰጣለሁ እንደ ሰው አይደለም ጌታዬ ልዩ ነው የተረሳውን ሰው እንዲህ ሚያስታውሰው አዝ:- ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection