የእግዚአብሔር ቤት ፈርሶ መሠዊያው ተድበስብሶ የእራስህን ቤት ትሰራለህ ስለ ወንጌል አይገድህ በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል ሁሉ የራሱን ድንጋይ ይክባል በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል ኤሎሂ ማን ይሻለናል? እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ ስለ ቤትህ የሚሳሳ ግድ የሚለው የወንጌል ነገር በጥቅም የማይጭበረበር ኤሎሂ (3x) አሃ ኤሎሂ የቀደሙት ሃዋሪያት ነቢያት ራሳቸውን ሰጡ እስከሞት ድረስ ዛሬ ራሱን ሚሰጥ ኧረ እርሱ ማነው የወንጌሉ ቅናት ውስጡን የበላው እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ ስለ ቤትህ የሚሳሳ ግድ የሚለው የወንጌል ነገር በጥቅም የማይጭበረበር ወንድም ለወንድሙ ማዘን ሲገባዉ ባደባባይ ላይ ክስ ዝንተላዉ ምንድን ነው እውነቱ ከተቀየረማ ከቀለላ ዋጋው ክርስትና ምንድን ነው የሚሻለን ኤሎሂ መፍትሄ ስጠን እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ ስለ ወንድሙ የሚሳሳ ግድ የሚለው የፍቅር ነገር በውሸት የማይወነጅል ኤሎሂ (3x) አሃ ኤሎሂ ትውልድ ሲተራመስ በራሱ መንገድ ላይ ግማሹ ወደታች ግማሹ ወደላይ ወዴት እንደምሄድ ትውልድ አላወቀም የዛሬን እንጂ የነገን አላየም (2x) እግዚአብሔር ሆይ ሰው አስነሳልን መንገድህን የሚያሳየን ቃልህን ብቻ የሚናገር በሁኔታ የማይጭበረበር ኤሎሂ (4x) የቀደሙት ሃዋሪያት ነቢያት ራሳቸውን ሰጡ እስከሞት ድረስ ዛሬ ራሱን ሚሰጥ ኧረ እርሱ ማነው የወንጌሉ ቅናት ውስጡን የበላው እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ ስለ ቤትህ የሚሳሳ ግድ የሚለው የወንጌል ነገር በጥቅም የማይጭበረበር እግዚአብሔር ሆይ ሰው አስነሳልን መንገድህን የሚያሳየን ቃልህን ብቻ የሚናገር በሁኔታ የማይጭበረበር ኤሎሂ (4x) የእግዚአብሔር ቤት ፈርሶ መሠዊያው ተድበስብሶ የእራስህን ቤት ትሰራለህ ስለ ወንጌል አይገድህ በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል ሁሉ የራሱን ድንጋይ ይክባል በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል ኤሎሂ ማን ይሻለናል? እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ ስለ ቤትህ የሚሳሳ ግድ የሚለው የወንጌል ነገር በጥቅም የማይጭበረበር ኤሎሂ (3x) አሃ ኤሎሂ ኤሎሂ (3x) አሃ ኤሎሂ