Song Lyrics

በታምራት

Bereket Tesfaye
Like Kahine
ለእኔ ቀኑ ጨልሞ መስማት እንጂ ማየት አልችል ጥዋት ልለምን የወጣሁ መሽቶ በሰው ነው ምገባው ትንሽ ትልቅ መሪዬ የሰው ፍቃድ ማደሪያዬ የእድሜዬን ግማሽ ቆጠርኩ ጨለማውን ለመድኩ መጣ ኢየሱስ ይሄ የአለም ብርሃን ዓይኖቼን ከፈተ በእውርነቴ ሃገር ታሪኬ ተለወጠ (2x) የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተከፈተ ብርሃኔ መልካምነቱን አየሁት በዚህች በአጭሯ ዘመኔ ተጥዬ የነበርኩ ያምስኪኑ እኔ ነኝ መንገደኛ የማያየኝ አሳዛኝ ሰው ነበርኩኝ በሃጥያቱ ወደቀ በ እግዚአብሔር ደቀቀ ብለው ሰዎች ፈርዱ ስብራቴን ሳይረዱ ደጉ ጌታ ከሰማይ አየኝ ከውድቀቴ አነሳኝ ቁስሌን ፈውሶ አከበረኝ መልሶ (2x) በታምራት የሚያኖረኝ አምላክ አለኝ የሚያስብልኝ የመቆሜ ምክንያቱ የ እግዚአብሔር ምህረቱ ባልጋዬ ላይ ተኝቼ ለአመታት ሸትቼ መልዐኩ ሲያናውጠው ማን ሊከተኝ ወደ ውሃው ዘመድ አዝማድ የለኝ እኔ የምለው ሚረዳኝ ቀርቦ ችግሬን አየና ተራመድ ሂድ ተነሳና ያለው ጌታ ለካ ዘመዴ ነው ስለ እኔ የሚሰማው ሽባነቴን ሽሮ አቆመኝ ቀይሮ(2x) በታምራት የሚያኖረኝ አምላክ አለኝ የሚያስብልኝ የመቆሜ ምክንያቱ የ እግዚአብሔር ምህረቱ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection