Song Lyrics

አፈታሪክ አይደለም

Bereket Tesfaye
Like Kahine
አፈ ታሪክ አይደለ ወይንም ተረት የኢየሱሴ ኃይልና ብርታት ጌታ አሁንም በሥራ ላይ ነው የሚያግደው እስኪ ማነው የተፈጥሮ ሕግ አያግደው ጌታችን ከሁሉ በላይ ነው የማይበገረው አንበሳ ኢየሱስ ከሞት ተነሳ የበላይ ኢየሱስ የበላይ (4x) አዶናይ ኢየሱስ የበላይ (4x) ኃያላን በሞት ሲሻሩ አልቻሉም መቃብር ቀሩ ኢየሱስ ግን የይሁዳ አንበሳ አሸነፈ ሞትን ድል ነሳ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ኢየሱስ ገኖ የሚታይ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ውድዬ ገኖ የሚታይ የንጋት ኮከብ ብርሃን ጌታ ኢየሱስ ለዘለዓለም (ነው (3x)) ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚያበራ የእኔ ኢየሱስ ባለ ግርማ (ነው (3x)) ማኅተሙን በአንዴ የፈታ የእኔ ኢየሱስ ብቸኛ ጌታ (ነው (3x)) ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ኢየሱስ ገኖ የሚታይ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ውድዬ ገኖ የሚታይ ባሕር ላይ የሚራመደው የቱ ጀግና ነው የሚሞክረው የእኔ ኢየሱስ ውኃ አይዘው ይራመዳል እንደፈለገው አዶናይ ኢየሱስ የበላይ (8x) አፈ ታሪክ አይደለ ወይንም ተረት የኢየሱሴ ኃይልና ብርታት ጌታ አሁንም በሥራ ላይ ነው የሚያግደው እስኪ ማነው የንጋት ኮከብ ብርሃን ጌታ ኢየሱስ ለዘለዓለም (ነው (3x)) ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚያበራ የእኔ ኢየሱስ ባለ ግርማ (ነው (3x)) ማኅተሙን በአንዴ የፈታ የእኔ ኢየሱስ ብቸኛ ጌታ (ነው (3x)) ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ኢየሱስ ገኖ የሚታይ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ውድዬ ገኖ የሚታይ የተፈጥሮ ሕግ አያግደው ጌታችን ከሁሉ በላይ ነው የማይበገረው አንበሳ ኢየሱስ ከሞት ተነሳ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ኢየሱስ ገኖ የሚታይ ከፍ ያለ በከፍታ ላይ (3x) ውድዬ ገኖ የሚታይ የንጋት ኮከብ ብርሃን ጌታ ኢየሱስ ለዘለዓለም (ነው (3x)) ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚያበራ የእኔ ኢየሱስ ባለ ግርማ (ነው (3x)) ማኅተሙን በአንዴ የፈታ የእኔ ኢየሱስ ብቸኛ ጌታ (ነው (3x)) የበላይ ኢየሱስ የበላይ (4x) አዶናይ ኢየሱስ የበላይ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection