Song Lyrics

ቃል አለኝ

Bereket Tesfaye
Like Kahine
ፈውሱን ፍልጌ ስንከራተት መፍትሄ አጥቼ ስባትት አንዴ ወደዛ አንዴ ወዲህ ስል እሩጬ ሩጬ ልቤ እስኪዝል ከዚህ ሁሉ ጣጣ የገላገለኝ የዳዊት ዘር ነው ቃልን የሰጠኝ በአንዲት ቃል ብቻ ተገላገልኩ ተባረክ ብዬ አመሰገንኩ አዝ፦ ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (2x) (ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል (ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል (ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው (ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው ቃል አለኝ (5x) ከጨለማ ውስጥ እኔን የጠራኝ አስደናቂውን ብርሃን ያሳየኝ የተናኩትን ና ብሎ ጠርቶ በወንጌል ዘይት ራሴን ቀብቶ የሚያየኝ ሁሉ እስኪገረም አቆመኝ ጌታ ለምስክር እንደ መልካሙ እንደዛ መሬት ቃሉን ዘራብኝ አረኩኝ ሀሴት አዝ፦ ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (2x) (ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል (ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል (ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው (ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው ቃል አለኝ (5x) እንደ አብርሃም በድንቅ የጠራኝ ሁሉንም ተወው ውጣ አትፍራ ያለኝ እስከ ዓለም ፍጻሜ ከእኔ ጋራ ነው የቃሉ መንፈስ በውስጤን ያለው ስለዚህ አልፈራም አልሸበር ድምፅን ሰማሁኝ ከእግዚአብሔር ወድቄ የምቀር መቼ ሆንኩና ጌታ ነግሮኛል ሄዳልሁ ገና አዝ፦ ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (2x) (ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል (ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል (ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው (ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው ቃል አለኝ (5x) (ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል (ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል (ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው (ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው ቃል አለኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection