Song Lyrics

ዕድሜዬን

Bereket Tesfaye
Like Kahine
ዕድሜዬን በሙሉ ብሰጠው አይቆጨኝም በመስቀል ደሙን ላፈሰሰልኝ ሰው ሁሉ ንጹህ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ በምድር ላይ እኔ ብቻ በኀጢአት ብበላሽ መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን ኢየሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር አዝ:- እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ ኦ ስለዚህ እኔ አመልካለሁ ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው ክፉ አመሌን አይቶ ከቶ ያልሰለቸው አስቸጋሪ ባሕሪዬ ልቡን ያላራደው በፍቅሩ አሸነፈኝ የራሱ አደረገኝ የማይገባኝን ክብር አለበሰኝ አዝ:- እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ ኦ ስለዚህ እኔ አመልካለሁ ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው ዕድሜዬን በሙሉ ብሰጠው አይቆጨኝም በመስቀል ላይ ሞቶ ራሱን ለሰጠኝ አዋርዳለሁኝ ሁለንተናዬን ለእርሱ ዳግም ወዶኛልና ኢየሱስ ንጉሡ የፍቅር ትርጉም የገባዉ ኧረ ማነው ሚገልጸዉ የአፍቃሩ ትርጉም ማነው እርሱ ኢየሱስ ያልራራ ለነፍሱ (2x) አዝ:- እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ ኦ ስለዚህ እኔ አመልካለሁ ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection