Song Lyrics

አለ

Yohanes Sisay
Special Edition
በእርግጥ አይሏል ማእበሉ ቅጥሏል ብሶ ትግሉ አማራጭ ተስፋ ሲጠፋ ጊዜውም ሄደ እየከፋ መጠጊያ ከለላ ቢፈለግ ሁሉም ሚገባበት ቢያጣ ከማዶ በባህሩ ላይ እየተረማመደ መጣ አይዟቹ አትፍሩ እኔ ነኝ ያለው የባህሩ ጌታ ጸጥ አድርጎ ሁሉንም ማእበሉን ከመንገዴ ገታ ትናንት ዛረ ዘላለም ያው ነው አይለወጥ ጌታ አለ በዙፋኑ ላይ የኔንም ችግር ሊፈታ *2 አለ አለ የኔ አባት አለ ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ ለነገም ተስፋየ እሱ ነው ዝም ብዬ አመልከዋለው ተስፋ ሲጨልም ቀኑ ሲመሽ የተደገፉትም ሲሸሽ ብቸኝነቱም ሲበረታ መኖርም ትርጉም ያጣ ለታ ሸክም ከብዶ ሲያንገላታ ድካሙ እጅግ ቢበረታ ወደ እኔ ያለው ኢየሱስ እረፍት የሚሰጥ ያለአፍታ እኔ ካንተጋ ነኝና አትፍራ ብሎኛል ጌታ ሸክሜን ያራገፈው ቀንበሬን ከላዬ እየመታ ተስፋዬን አድሶ ያቆመኝ እሱ ነው የነፍሴ ቤዛ ታሪኬን የቀየረው እንድኖር በሱ ታዛ ህይወቴን የቀየረው እንድኖር በሱ ታዛ አለ አለ የኔ አባት አለ ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ ለነገም ተስፋየ እሱ ነው ዝም ብዬ አመልከዋለው አለ በዙፋኑ ላይ የተጨነቀ የሚያይ አለ ማደሪያው አርጎኛል ውዱ መንፈስ ቅዱስ አለ በዙፋኑ ላይ የተጨነቀን ሚያይ አለ በክብር ግርማው ላይ በአብቀኝ በሰማይ አለ ደሞ በእኔ ውስጥ የነገስታቱ ንጉስ አለ ማደሪያው አርጎኛል ውዱ መንፈስ ቅዱስ አለ አለ የኔ አባት አለ ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ ለነገም ተስፋየ እሱ ነው ዝም ብዬ አመልከዋለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection