የዘላለም ደስታዬ ነህ የዘላለም እረፍቴ ነህ ባንተ ደስታ ሆነልኝ መልካም ነህ ባንተ እረፍት ሆነልኝ መልካም ነህ ባንተ ሰላም ሆነልኝ መልካም ነህ እንዴት እረሳለሁ ያለፈውን ሁሉ አስታውሰዋለሁ በረሀ ሀሩሩን ከየት እንዳነሳኸኝ መቼም አረሳውም ታሪኬ ብዙ ነው ብናገር አያልቅም ዛሬ ደግሞ አልፎ በመልካምነትህ ይኸው ዘምራለው አምሮብኝ በቤትህ እድሉን ካገኘው ፀጋህ ከበዛልኝ ገና እዘምራለሁ ጌታ ክበርልኝ ገና እዘምራለሁ ጌታ ክበርልኝ የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ብቻ መች ይመስል ነበር እንደዚህ የሚሆን ክንድህ ባትረዳኝ ከእኔ ጋር ባትሆን እኔ ያላመሰገንኩ ማን ሊዘምርልህ ኢየሱስ እላለሁ በቀረኝ ዘመን ኢየሱስን እዘምራለሁ መልካምነትህን ለአለም አወራለሁ መድኃኒቴ እወድሃለሁ መልካምነትህን በአይኔ አይቻለሁ/X2 የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ብቻ