Song Lyrics

ያዘኝ

Yazegn

TSEBAOT TSEGAYE
Special Edition
እኔን መታገል አልችልም በራሴ ሞክሬ ወደቅኩኝ አድክሟታል ነፍሴ ነገር ግን አለና ከእኔ የበረታ እርሱን ስሻው አለሁ እልሀለሁ ጌታ እኔን መታገል አልችልም በራሴ Chorus ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ ለአፍታ ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ Verse 2 የተከበብኩበት እሾኹ ነው ብርቱ የዚህ ዓለም ኃሳብ የማያልቅ ምኞቱ ላቆጥቁጥ ስል ደርሶ ፈጥኖ እንዳያንቀኝ ቀድመህ ድረስና ልቤን ለም አድርግልኝ Chorus ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ ለአፍታ ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ Verse 3 እለምንሀለሁ እንድትሰማኝ አባ ጸጋህ ካላገዘኝ ጨለመብኝ በቃ ስጋና ስሜቴ እንዳይመራ ሕይወቴን ቶሎ እርታኝ እና ባርክልኝ ዘመኔን እኔን መታገል አልችልም በራሴ Chorus ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ ለአፍታ ከእኔ በላይ ጸጋህ የበረታ ይያዘኝ ሳይለቀኝ አይልቀቀኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection

More from TSEBAOT TSEGAYE