Song Lyrics

ወደድከኝ

Wededkegn

TSEBAOT TSEGAYE
Special Edition
በጣር በበዛ ስቃይ በነፍስ ድካምህ አባትህ ጨከነ ፊቱን አዞረብህ ለወጉህ እየማለድክ ውርደት ላለበሱህ ቁጣውን አበረድክ እጅጉን ለጠሉህ ቸር የሆንህ በምህረትህ ባለጠጋ አንድም የለም ካንተ ፍቅር የሚጠጋ የቆሰልህ የተበሳህ ልታርቅ ነው ከእኔ አበሳ ፈውሴ ነህና 2x ብቸኛ መዳኛ 2x ኢየሱስ ብቸኛ 2x ከሕይወት ልታደርሰኝ ደምህ ጎረፈ መስዋእትነትህ ውድቀቴን አለፈ ፀጋህ ፈሰሰልኝ ተደግፌው ቆምኩኝ ላትሰርዝ ላትተወኝ አንዴ ወደድከኝ 3x አንዴ መረጥከኝ3x ማነው ሚለየኝ3x አንዴ ወደድከኝ3x የማልወጣበት ከመሰለኝ እንዳልንቀሳቀስ ጠፍሮ ከያዘኝ እራሴን ካወረድኩበት ከከተትኩበትም አዘቅት ክንድህ ይደርሳል ከሲኦል አይርቀውም እኔን ለማስጣል እልፎቹን በጎች እየተወ አንዷን እኔን ሲል ከነፈ ቸር የሆንህ በምህረትህ ባለጠጋ አንድም የለም ካንተ ፍቅር የሚጠጋ የቆሰልህ የተበሳህ ልታርቅ ነው ከእኔ አበሳ ፈውሴ ነህና 2x ብቸኛ መዳኛ 2x ኢየሱስ ብቸኛ 2x የማይነጥፍ ጅረት ነው ፍቅርህማ ውዴ ቃልህን ፈፀምከው እንዳትጥለኝ አንዴ በድካም በዝለት እጅግ እየበረታ በአብ ፊት መታያ ይኸው ሆኖልኛል እኔን ልታነግሰኝ ዋጋ የከፈልከው በጌቴሴማኔ ነፍሴን ባንተ ያረከው በሕይወት ኑሪ ያልከኝ ማቄን ቀደህክኝ አንዴ ወደህ መረጥከኝ ይህ ነው መልሕቅ የሆነኝ አንዴ ወደድከኝ 3x አንዴ መረጥከኝ3x ማነው ሚለየኝ3x አንዴ ወደድከኝ3x
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection

More from TSEBAOT TSEGAYE