Song Lyrics

ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ

Shewaye Damte
Special Edition
አዝ፦ ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆም ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል(፪x) እርካታን ይሰጣል የሰው ልጅ ባከማቸው ንብረት ሰላምን አግኝቶ ቢሆን ኖሮ አይሰማም ነበር ከዓለም የሃዘን እንጉርጉሮ ከጌታ ጋር ያከማቸ እርሱ ይሰበስባል የያዘው የረዘዘው ሁሉ እርካታን ይሰጠዋል አዝ፦ ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆም ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል(፪x) እርካታን ይሰጣል ወርቅ አንጥፈው አልማዝ ደርበው ብርን ተንተርሰው ቢተኙትም የእረፍት ጌታ ኢየሱስ ከሌለ የሰላም እንቅልፍ የለም ጌታ እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ የሰው ድካም ከንቱ ነው ዘለቄታ ያለው ሰላምና በረከት ከእግዚአብሔር ነው አዝ፦ ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆም ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል(፪x) እርካታን ይሰጣል በዓለም ፍፁም ገነው ቢታዩም ጽኑ ክቡር ሃያል ቢባሉ የመንፈስ እረፍት አይገኝም ካልመጣ ከመስቀሉ ግባ መሬት አይቀርምና በሞት ጥላ ማለፉ ሰው በጌታ ኢየሱስ ካልዳነ የእሳት ባሕር ነው ትርፉ አዝ፦ ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆም ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል(፪x) እርካታን ይሰጣል እኔስ በኢየሱስ ሰላም አለኝ ሆኜ ሳለሁኝ ምስኪን ድሃ ነፍሴን ዕለት ዕለት ያረካታል በጣፋጭ የሕይወት ውሃ በምድርም ሳለሁኝ ይመስገን ለነፍሴ ዋስትና አላት ድንኳኔም ቢፈርስ ጌታ ይክበር አለኝ የከበረ ቤት አዝ፦ ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆም ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል(፪x) እርካታን ይሰጣል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection