ከላይ ሰማይ የሚቀዳ ያንተን ቤት ንፁህ ውሃ ነፍሴ ወዳ ቃልህን ልትሰማ መፅሀፍህን ከፍታ መንፈስ አግዘኝ ትልሀለች ብርሀንህን ሽታ ነፍሴ ተርባሃለች አንተን ብላ መፅሃፍህን ይዛለች ሌላ ሁሉን ጥላ 1. ልጅህን በማመን መዳን እንዳገኝበት ጥበብ በሚሰጡኝ ቅዱሳኑ መፅሃፍት ነፍሴ ተርባሃለች በፍፁምና በጎ ስራ መፅሃፍህን ይዛለች አንብቤ ፍሬን እንዳፈራ በመማርና በመገሰፅ ልቤን በማቅናት ነፍሴ ተርባሃለች በፅድቅም ባለ ምክርህ እንድቆም ከላላሁበት ነፍሴ ተርባሃለች 2. ልጅህ በልቤ ላይ ደምቆ እስኪወጣ በጨለማ እንዳለ መብራት ቃልህን አልጣ ነፍሴ ተርባሃለች በቅዱሳንህ መልዕክት መፅሃፍህን ይዛለች ነድተህ ያፃፍከውን እውነት በቂ በሆነው ቃል ህፀፅ አልባ ባለስልጣን ነፍሴ ተርባሃለች ባልተጣረሰ እውነት እንድትመራ መንገዴን ነፍሴ ተርባሃለች