Song Lyrics

ሙሉ ቤት

Mulu bet

Mekuanint Samuel
Gosquala Sew
ያን ጉባኤ አያለው ያንኑ ሙሉ ሰው ሁሉ በአንድነት ገብቶ ወደታነፀው ልቤ ለዚያ ፅኑ ነው ዛሬ እንኳ ባይደላው አልከፋም በዚያ ሁሉን እረሳለው 1. ተጠላልፎ የወደቀው የምድር ህይወት ድካም ነው ማን ተስፋ ሊያረገው ነገው እንፋሎት ነው አዬ በጥቂት መዛሌ ደክሜ መሰበሬ ተስፋዬ በላይ እንጂ በዚህ አይደለም ክብሬ ከቀናቴ ደመና ከፍ ልበልና ልታገስ ደጅም ልጥና ተስፋዬ ቀርቧልና ውርደት ሀጥያት ውድቀት ከቶም የሌለበት ውዴ ራስ የሆነበት ናፍቆኛል ያ ሙሉ ቤት ያን ጉባኤ አያለው 2. ስጋ ተዋርዶ ሲዘራ መች ይመስላል ሚነሳ እንኳን ሰዉ ላይከብር አይቀርም ዛፍ እንስሳ ሞት እንደው ልማዱ ነው ስንቱን ከእኛ ወሰደው ያ ቀን ግን በደጅ ነው ትንሳኤ ሊሆን ነው በጌታ ያመነ ሰው ቢሞት መች ጎደለ ዘለዓለም በታመነ በእርሱ እቅፍ ታደለ ያንን ቀን የናፈቀ ዘይቱንም የሰነቀ ይዘጋጅ የጠበቀ በአየር ላይ ተነጠቀ ያን ጉባኤ አያለው 3. አንዳንዴ ብርታት ይከዳል ሁለንተናም ይጎዳል ስጋ ነፍስን ስትወጋ መንፈስ ይጠመዳል ያን ጊዜ ከሳሽ ይቀርባል ፍላጻውን ይልካል ግና በእንብርክክ ሳለው አባቴ ፈጥኖ ይደርሳል ይኸው ዘምራለው ሚዋጋልኝ እርሱ ነው በእቅፉ እንዳለው ሩጫዬን ጨርሳለው አይዞኝ ጥቂት ጊዜ ነው ስጋዬም መታደሱ ነው አባቴን የማየው ወይ ዛሬ ወይ ነገ ነው ያን ጉባኤ አያለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection