ጉዳይ ሳይኖረኝ መጣለሁ ፊትህ ጉዳዬ ሆነህ ላመልክህ ምክንያት ሳይኖረኝ መጣለሁ ፊትህ ምክንያቴ ሆነህ ልሰግድልህ ምንም ሳልፈልግ መጣለሁ ፊትህ አንተን ፈልጌ ልገዛልህ ስለፈውሴ አይደለም እስራቴ እንዲፈታ በቃ መጥቻለሁ አንተን ፍለጋ ላመልክህ ልገዛልህ ልሰግድልህ ጠይቅ ብባል ጥያቄ አለኝ ስጠኝ ማለት አያልቅብኝ ግን ለዛሬ ሁሉ ይቅርብኝ የአባቴ ፊት ነው ያማረኝ በቃ ዝም ብሎ ማምለክ አሜን ተባረክ ማለት ይኸው የልቤ ጥማት ከእግሩ ስር ልስገድለት ፍለጋዬ ያለምክንያት ያለሰበብ አንተን ማግኘት ዙፋንህ ስር ልንበረከክ ሳላቋርጥ አንተን ላመልክ