በዚች ምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አለብኝ እኔ ዝም አላለሁ አንተ ተዋጋልኝ አንተን ያሰለፉ ሰልፉ ሰምሮላቸው አይቼ ተምሬያለሁ ከድል ዝማሬያቸው ዝም ብዬ አቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ እለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (፪x) ሰልፉ የእኔ መስሎኝ እረታለሁ ብዬ በሥጋዬ ስታገል ተዝለፍልፌ ዝዬ መረታቴነውኮኢየሱስ ጌታዬ ኧረ ቶሎ ናልኝ አይብዛ መከራዬ ዝም ብዬ አቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ እለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (፪x) የእሳት ሰረገላው መለኮታዊው ጦር የድምፅህ ነጐድጓድ ጠላት የሚያሸብር ይምጣ ይዋጋልኝ እኔ ኃይል የለኝም አሁን አውቄያለሁ ሰልፉ የእኔ አይደለም ዝም ብዬ አቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ እለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (፪x)