ብዙ አብረን መጥተናል አሁን ተስፋ እንዳልቆርጥ ድምፅህ አልተለወጠም ከጉያህ እንዳልሮጥ ባይህ ባይህ ሁኔታ እንጂ አንተ አልተለወጥክም እንዳልከስህ ሰበብ አጣሁ ጥፋት የለብህም ባይህ ባይህ ህይወት እንጂ አንተ አልከፋህብኝም እንዳላማህ እቅም አጣው ጎኔን አልለቀክም ወይ ውስጤ ቆርጦ አልቆረጠ ወይ ተስፋ አላደረኩብህ አንተስ ምን ትለኛለህ ኢየሱስ ልጠይቅህ ልመንህ አይደለ? መረቤን ልጣለው? ከዚያ ከሚመጣው እጥፍ እጠግባለሁ? እንጀራዬን በውሀው ላይ አምኜ ልጣለው? ተመልሼ ስመጣ ወይ አገኘዋለሁ? የአንተ አላማ ውብ ነው ይህንን አዉቃለሁ እቅድህ ሰፊ ነው በደንብ አውቃለሁ ግን እንዴት ትስማ ይህቺ ነፍሴ ዝምብላ ትሰጋለች ምትወድቅ ይመስላታል ለፍርሃት ትረታለች ወይ ውስጤ ይኸው ፀሎቴ በፊትህ ውስጤን አልደብቅ አልሸሽግህ የዘገየህ ቢመስል በእኔ ጊዜ ቀመር መኖርህን ልቤ ፍፁም አይጠረጥር ከነጎድጓድ በላይ ጮክ ብሎ ያወራል እኔ ፀጥ ካልኩኝ ዝምታህ ይሰማል ይኸው ፀሎቴ በፊትህ ውስጤ አይሸሸግ አልደብቅህ የዘገየህ ቢመስል በእኔ ጊዜ ቀመር መኖርህን ልቤ ፍፁም አይጠረጥር ከነጎድጓድ በላይ ጮክ ብሎ ያወራል እኔ ፀጥ ካልኩኝ ዝምታህ ይሰማል ዝም እላለው በፊትህ ፀጥ ጊዜው ደርሶ መልስ እስክትሰጥ አላወራም እላለሁ ዝም ፣ ዞር ብዬ አላማህም አዎን አምንሃለሁ መረቤን እጥላለሁ ከዚያ ከሚመጣው እጥፍ እጠግባለሁ እንጀራዬን በውሃው ላይ አምኜ እጥላለሁ ተመልሼ ስመጣ አዎ አገኘዋለሁ