ሰላም ሰላም ይሄው ሰላም ለሰው ልጆች ህይወት መዳን በምድር ቢሆን በሰማይ ማንም የለም ኢየሱስ ነው መካከል ቤዛ ለዓለም ሰላም ኢየሱስ ነው [3×] ሰላም የምኖረው በሱ ነው የምኖረው 2× የምመካው በሱ ነው የምመካው 2× የምኮራው በሱ ነው የምኮራው 1- የሰላሙ ጌታ እርሱ ተሸክሞኝ እንዳልነዋወጥ እየደጋገፈኝ እየከለከለ ሟርትና ቀስቱን አሸንፎልኝ አለፍኩት ስንቱን አልፈራም ይዞኛል ጌታ ኢየሱስ አሳርፎኛል የምኖረው በሱ ነው የምኖረው 2× የምመካው በሱ ነው የምመካው 2× የምኮራው በሱ ነው የምኮራው 2× 2- ከዚህ አለም ጭንቀት ከሞት ፍርሃት እንቅልፍ ካሳጣኝ በቀን በለሊት ቀንበሬን ሰብሮ ጨለማየን ገፎ ነፃ አወጣኝ ኢየሱስ ደርሶ አልፈራም ይዞኛል ጌታ ኢየሱስ አሳርፎኛል ሰላም ኢየሱስ ነው [3×] ሰላም 3- ጌታዬ የሰጠው ዘላቂ ሰላም ጊዜያዊ አይደለም ልክ እንደ ዓለም ሰው ሁሉ ወስዶ የማያልቅ እረፍት የሚትረፈረፍ ለሁሉም በእውነት ወገኔ ቀርቦልሃል በሁሉም ስፍራ ጌታ ይጠራሃል ተቀበለው ሰላምህ እሱ ነው ለዘለዓለም መኖሪያህም ነው ኢየሱስ ሰላሜ ሆኗል በልቤ ነግሶ ይኖራል አልሻም ከሱ ሌላ መታመኛ ዘላለም ሆኖኛል መኖሪያ ኢየሱስ ሰላሜ ሆኗል በልቤ ነግሶ ይኖራል አልሻም ከሱ ሌላ 4× እኔ አልሻም ከሱ ሌላ አልሻም ከሱ ልላ