Song Lyrics

ሙላኝ

Asrat Mekonnen
Special Edition
መንፈስ ቅዱስ ና ጌታ ህይወታችንን አበርታ በመገኘትህ(በህልውናህ) ጎብኘን እንደገና አግኘን (አግዘን) ውረድ ውረድብኝ በላዬ ሃልይልን አልብሰኝ ጌታዬ /2× አባቶች ላይ የወረደው ያ ክብር ትውልዴ (በእኔም) ደግሞም ይኑር /2× 1-በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው በሙላት ቃሉን መናገር እንዲቻላቸው እንዳይሰብኩ ከነበረው ብርቱ ዛቻ /2× የተወጡት በክብርህ ነው ባንተ ብቻ ሙላኝ/3× ጌታ መንፈስህን /2× መንፈስ ቅዱስ ና ጌታ ህይወታችንን አበርታ በመገኘትህ(በህልውናህ) ጎብኘን እንደገና አግኘን (አግዘን) ውረድ ውረድብኝ በላዬ ሃልይልን አልብሰኝ ጌታዬ /2× 2- ደረቁን ምድር ፍሬ እንዲያፈራ ከሰማይ ዝናብ ወርዶ እንደሚያረካ አንተ ከብረህ እንድትታይ ፈቅጃለሁ ከእግሮቼ እስከ ራሴ (ህያው ፍሬ እንዳፈራ) ሙላኝ ይኸው ሙላኝ/3× ጌታ መንፈስህን /2× 3- እስጢፋኖስ ፀጋንና ሃይልን ተሞልቶ ሲሰዋ ስለወንጌል ራሱን ሰጥቶ አባቶቼን ያበረታው ያንተ መንፈስ ይሄው ያበርታኝ እንድመሰክር ስለ ኢየሱስ /2×
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection