አትሰለቸኝም (×2) ቀን ከሌት ባመልክህ እሳት አለ ውስጤ ኦሆሆ አይደካክመኝም እሳት አለ ውስጤ አይደካክመኝም (×2) መንፈስህ አለ ውስጤ አይደካክመኝም (×2) እስር ቤት የማያስረው ጠባቂ ማይጠብቀው ቢጠረቅ ከላይ ከታች ለምንም የማይመች ተቀብሮ የማይቀር ፍቅር ፈንቅሎ ሚወጣ እሳት አደባባይ መድረክ ማይሻ የእግዚአብሔር ህልውና (×2) ህልውናህ (×6) ዓይኔ ነው የማይበት እግሬ ነው የቆምኩበት ሳቄ ነው የአንደበቴ መንፈስ ቅዱስ የልቤ ደስታ ወደላይ ከፍ የሚያደርገኝ እንደንስር የሚያበረኝ ከጎጆዬ ክልል ቀድሜ የምድርን ስበት አልፌ ወደ ሰማይ ህልውናህ (×6) አትሰለቸኝም (×2) ቀን ከሌት ባመልክህ እሳት አለ ውስጤ ኦሆሆ አይደካክመኝም እሳት አለ ውስጤ አይደካክመኝም (×2) መንፈስህ አለ ውስጤ አይደካክመኝም (×2) ከአልባስጥሮስ ሽቶ ይልቅ ውዴ ጠረኑ ከአለት ሚጠነክረው ፅኑውን የሰው ልብ በማዕበል እንደተመታ ውቅያኖስ ያናውጠዋል ኃያል ዝናውን ትቶ ጀግኖ ወገቡን ፈቶ ይከተለዋል ህልውናህ (×6)