Song Lyrics

የዜማ ጊዜ ደረሰ

Suraphel Demissie
Yezema Gize Derese
የዜማ ጊዜ ደረሰ ያለቀሰ እንባው ታበሰ ኢየሱስ መጣ ወደርሱ ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ ዘሬን ተሸክሜ እያለቀስኩ ሄድኩኝ ዛሬ ነዶ ይዤ ለክብሩ ዘመርኩኝ ለቅሶ ማታ ነበር ጠዋት ደስታ ሆኗል የአምላኬ ክብር በኔ ላይ ጨምሯል እራሴን ሰጥቼ ላምልከው ፈቅጄ ለኔ ፈጥኖ ደራሽ ኢየሱስ ወዳጄ እራሴን ሰጥቼ ላምልከው ፈቅጄ እንባየ ታብሷል በርሱ በወዳጄ የዜማ ጊዜ ደረሰ ያለቀሰ እንባው ታበሰ ኢየሱስ መጣ ወደርሱ ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ 2× ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ ዛሬማ ላሰማ እልልታ ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ክረምት አለፈ ዛሬማ ሀዘን ጨለማ ምድረበዳውና ደረቁ ምድር ደስም ይላቸዋል ሀሴት ያደርጋል ብሎ ያለው ቃሉ ዛሬ ተፈጽሟል ዲዳው ተፈውሶ ለክብሩ ያዜማል እራሴን ሰጥቼ ላምልከው ፈቅጄ ለኔ ፈጥኖ ደራሽ ኢየሱስ ወዳጄ እራሴን ሰጥቼ ላምልከው ፈቅጄ እንባየ ታብሷል በርሱ በወዳጄ ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ ዛሬማ ላሰማ እልልታ ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ክረምት አለፈ ዛሬማ ሀዘን ጨለማ ክረምቱ አለፈ አዲስ ዘመን መጣ ወይኖቹም አበቡ በለሱም ጎመራ ከአለት ንቃቃት ወጣሁ ልዘምር ማዳኑን ላወራ ድንቁን ልናገር የዜማ ግዜ ደረሰ ያለቀሰ እንባው ታበሰ ኢየሱስ መጣ ወደርሱ ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ ዛሬማ ላሰማ እልልታ ዛሬማ ግዜው ነውና ዛሬማ ላሰማ ዜማ ዛሬማ ክረምት አለፈ ዛሬማ ሀዘን ጨለማ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection