ከደዌ መፈወስ የተተወን ማንሳት ከብዙዎች ህይወት የሞትን ጣር ማጥፋት ለደከመዉ ብርታት ለሰዉ ልጆች መፍትሄ ሁሉንም የምችል በሰዉ መኃል ታየ መንደሩ ስገባ በወገኑ ይገፋል ሚቀበለዉን አጥቶ እጅግ በጣም ያዝናል ክብር እየተገባዉ ክብር አልተሰጠዉ እንደ ሰዉ ልጅ ታየ እግዚአብሔር የላከዉ እንደ ሰዉ ቢቀርበኝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ እኔ ቢመጣ ከላይ ከሰማይት ከከበረ ስፍራ ወርዶ /ከላይ/ እንደመጣ ይህንን አምናለዉ እኔ እቀበላለዉ መንደሬ ቢገኝም እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነዉ እኔን ሊያድን ብሎ በደዌ ቢደቂም ሰዉ ብቻ ነዉ እሱ ብዬ አልታለልም እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነዉ ከጥንት የከበረ ማንም ሳይኖር በፊት ቀድሞ የነበረ ፍትረት ሳይፈጠር ቀድሞ ከጅምሩ በሰማይ ቀላይት ወንዞችም ሳይኖሩ ያኔ ከአባቱ ጋር በሰማይ ነበረ ከአብ ሊያሰታርቀን ሊያድነን ወረደ ኢየሱስ ፬× እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነዉ ከጥንት የከበረ ማንም ሳይኖር በፊት ቀድሞ የነበረ