Song Lyrics

በብርሃንህ

Meron Alemu (Judy)
Special Edition
የከበበኝ ጨለማ ተስፋ የማጣት ደመና የጋረደው ትኩረቴን ብዥ ያረገው መንገዴን አንተን ሳስብ ይገፈፋል ፅልመቴ ወገግታ ይሆናል ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃንህ እጓዛለሁ ጨለማዬን አሸንፈሀል በብርሃንህ ብርሃን አየሁ አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ ወደ አንተ እጠርጋለሁ ፊትህን እሻለሁ እፈልግሃለሁ አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ ወደ አንተ እጠርጋለሁ ኢየሱስ እላለሁ እፈልግሃለሁ ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃን እጓዛለሁ ጨለማዬን አሸንፈሀል በብርሃን ህ ብርሃን አየሁ 2x አንተን ሣስብህ ልቤ ይበረታል የቃልህ እውነት ተስፋን ይሰጠኛል ዛሬም ነገም እታመንሃለሁ በብርሃንህ ውስጥ ብርሃንን እያየሁ አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ ወደ አንተ እጠርጋለሁ ፊትህን እሻለሁ እፈልግሃለሁ አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ ወደ አንተ እጠርጋለሁ ኢየሱስ እላለሁ እፈልግሃለሁ ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃን እጓዛለሁ ጨለማዬን አሸንፈሀል በብርሃንህ ብርሃን አየሁ 2x በብርሃንህ ብርሃን አየሁ Ps 36:9
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection