Song Lyrics

ለኔ ነው

Lidia Anteneh
Special Edition
እንዴት ያለውን ፍቅርህን ነው ያደልከን የማይነጥፈው ሰላምህን ያካፈልከን እንዴት ያለውን ምህረት ነው ያገነንከው ለጠፋሁትኝ መስዋዕት ሆነህ የቀረብከው እንዴት ያለውን ክብር ነው ያለበስከን በፀጋህ ብዛት ድህነትን ያጎናፀፍከን እንዴት ያለውን ውስጣዊ ሰላም ደስታ አበዛህልኝ ጋረድከኝ ከአለም ሁካታ የአባትህን ፍቃድ ልትፈፅም ነው ፍፁም ታዘህ አቀረብከኝ ዳግም ወደ ራስህ ቤዛ ሆነህ አንተ የኔ አባት እኔም ያንተ ልጅ ሆኛለው ማንም ላይለየን ኪዳናችን በቅዱስ ደምህ ነው ፅድቅ አልብሰኸኝ ኩነኔን ከኔ አርቀኸዋል የሚከስኝ የለም አንዴ ወደህ መርጠኸኛል ታማልዳለህ ልታኖረኝ በፅድቅ ህይወት ዘመኔን ከብረህ ዘላለሜን በውበት ልትታይበት ለኔ ለኔ ነው ይህንን ሁሉ የሆንከው ለኔ ብለህ ነው ደምግባትህን ውበት ያጣኸው አዎ ለኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው ኢየሱስን በማወቅ ወደሚገኝ በረከት ይኸው ገባሁኝ ፅድቅ ሆነህልኝ በእምነት ስለክብሩ ልኖር ተሾምኩኝ እንደመልካም ልጅ በክብር ስም ተጠራሁ ተያዝኩኝ በአንተ እጅ ለምን ወደድከኝ ስለራሴ ይገርመኛል ከኔ አንዳች የለም አውቃለሁ ይህ ገብቶኛል እንደምትወደኝ ለሞት ታዝዘህ አሳይተሃል አቤት እላለው ከአይምሮዬ በላይ ሆነህብኛል ለኔ ለኔ ነው ይህንን ሁሉ የሆንከው ለኔ ብለህ ነው ደምግባትህን ውበት ያጣኸው አዎ ለኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection