ለጻድቅ ሰው እሚሞት ምናልባት ይገኛል በጭንቅ ይገኝ ይሆናል በምጥ ለእኔ መሞትህ በህይወቴ አድርጎሃል ብርቅ አደረገህ ብርቅ ብርቅ ነው ድንቅ ነው አስቤም አላውቀው አልሜም አላውቀው አቅጄም አላውቀው የኔማ ውድ ነው የኔ እጅግ ድንቅ ነው ከሰላውም ስለት ማምለጤ በእርሱ ነው ማነው ለጠላቱ የሚሰጥ ህይወቱን ጌታዬ ሆነልኝ ሰጠኝ ማንነቱን አዝ አለኝ ያልኩት እኔስ ከሁሉ ያስበለጥኩት ልቤ አርፎ እፎይ ብሎ የተማመንኩበት በክርስቶስ ያኔ የሰራልኝ ስራ እርሱ ነው የሚያኮራኝ አርጎኝ ከአብ ጋራ አዝ እንደዚህ ነው ለካ መች ገመተው ልቤ ተፈጸሞ አልቆ ደርሷል አጠገቤ ለእኔ እንደሆንክልኝ እንደበለጥክብኝ መድኃኒትነትህን አለም ይወቅልኝ ለእኔ እንደሆንክልኝ እንደበለጥክብኝ መድኃኒትነትህን ፍጥረት ይወቅልኝ መታሰሩ መገፋቱ መውደቅና መነሳቱ ይሄ ሁሉ ለእኔ ነው አሃ የእንጨት መስቀል መሸከሙ ያፈሰሰው እንባ ደሙን ይሄ ሁሉ ለእኔ ነው (5) መታሰሩ መገፋቱ መውደቅና መነሳቱ ይሄ ሁሉ ለእኔ ነው አሃ የእንጨት መስቀል መሸከሙ ያፈሰሰው እንባ ደሙን ይሄ ሁሉ ለእኔ ነው (17)