Song Lyrics

ፍለጋዬ

Flegaye

አንተን መፈለግ አይደለም ምርጫ ግዴታዬ ነው ለምን ከተባለ ህይወት ነህና እንድኖር ነው (3×) ስውር ሆነህብኝ አይደለም አንተን መፈለጌ ይበልጥ እየጓጓው ልቦናዬን ባንተ ላይ አድርጌ ከኔው ጋር እያለህ አብዝቼ እሻለው ፍለጋዬ ሁሉ ፈላጊዬ ላይ ነው። አንተን መፈለግ አይደለም ምርጫ ግዴታዬ ነው ለምን ከተባለ ህይወት ነህና እንድኖር ነው (3×) ፍለጋ ስጀምር እየሱሴ ስልህ ትመጣለህ እያልኩ በምናብ ስስልህ አርፌ እገኛለው በመፈለጌ እንኳን ሳትከፍትልኝ በሩን ቀርቤ ሳንኳኳ አንተን መፈለግ አይደለም ምርጫ ግዴታዬ ነው ለምን ከተባለ ህይወት ነህና እንድኖር ነው (3×) አሳ ከውሃ ካልተዋደደ ላለመኖር እንደፈቀደ ዛፍም ከመሬት ስሩን ካልሰደደ ላለመፅናት እንደወደደ ሰውም እንዲሁ አንተን ካልፈለገ በራሱ ፈቃድ ሞቱን አሳደደ(አፋጠነ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection