Song Lyrics

ልቤን ደስ ይለዋል

Henok Hatiya
Special Edition
ልቤን_ደስ_ይለዋል *2 ልቤን እንዲሁ ሳስበው #መዳኔን *3 ቆም ብዬ ሳስበው #መትረፌን *3 እንደ ቀልድ አይደለም ፣ መትረፌ መዳኔ ደም ተከፍሎልኛል ፣ በጉ ታርዷል ለኔ ባርነቴ ቀርቶ ፣ ወራሽ ልጅ ሆኛለሁ በኢየሱስ ድንቅ ስም ፣ አምኜ ድኛለሁ አሁን በክርስቶስ ፣ ኩነኔ የለብኝም ከጸጋው በታች ነኝ፣ኃጢአት አይገዛኝም ኢየሱስ ሆኖልኝ ፣የዘላለም ጽድቄ ድፍረት አግኝቻለሁ ፣በደሙ ታርቄ አንገቴን ላልደፋ ፣ ቀና ቀና አርጎኛል በጠላት ቀጠና ፣ በድል አራምዶኛል በደሙ አስወገደው ፣ ኃጢአቴን ከኔ ላይ ምን አለ 'ሚያስመካ ፣ ከልጅነት በላይ ዳግም ተወልጄ ፣ ከማይጠፋ ዘሩ ላልጠፋ ድኛለሁ ፣ አብ ስቦኝ በፍቅሩ አሁን ድፍረት አለኝ ፣ ለመቆም በፊቱ በሰራልኝ ስራ ፣ በመስቀል ላይ ሞቱ #ቀና_እላለሁ_ቀና_ልጁ_ነኝና_ቀና *2 #ቀንበር_ተሰብሯል_ቀና *2 ባርነት የለም ቀና ቀንበር ተሰብሯል ቀና ባርነት የለም ቀና ልጁ ነኝና ቀና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection