Song Lyrics

አይቀልብኝም

Hamlet Beljun
Special Edition
አንተ ቀርበህ እንጂ በመንገዴ አልደርስብህም ፀጋህ በምነት እንጂ በስራዬ አልፀድቅም ማለቂያ በሌለዉ ፍቅር ማባሪያ በሌለዉ ምህረት ፍፁም አይቀልብኝም ስትመጣ ወዳለሁበት በሚገባኝ ቋንቋ በኔ አነጋገር ወርደህ ያስረዳኸኝ የፈቃድህን ሚስጥር ፍቅር ግድ ብሎህ እንጂ ወደታች ያየኸው አንዳች አይጎልህም የለም ምጨምረው አይቀልብኝም ፍቅርህ አይቀልብኝም አይቀልብኝም መዉደድህ አይቀልብኝም ስትችል መኖር ያለ እኔ እኔን የፈለከዉ በምስልህ እንደ ሠዉ ተገኝተህ ራስህን ባዶ ያረከዉ በላይ ያለዉን ክብርህን ትተህ በዉርደት ያለፍከዉ ደምግባት ዉበትህን ያጣህ ህይወቴን ልታተርፋት ነዉ ከምንም ከማንም ትበልጥብኛለህ ወደኔ ቀርበህ ስትመጣ ልቤ አያቀልህ ገኖልኝ ምህረትህ ተቀብሎኝ ፊትህ ስትሰነብት ቤቴ በዝቶ ትእግስትህ ገና ሳልናገር ቃላቴን አዉጥቼ ደሞም ሳልገልጠዉ የልቤን አዉግቼህ የዉስጤ ሲገባህ መሻቴን ስትፈፅም ይህ ሁሉ እንዲገባኝ ፍፁም (አልቆጥረውም)*2 ካገኘኝ ይህ ሁሉ በጎነት ተገብቶኝ የተቀበልኩት የለም አለምድህ መድኔ አንተ እኮ ብርቅ ነህ ለኔ ዛሬም በልቤ እንደተፈራህ እንደተከበርህ አለህ ባወኩህ በተጠጋሁ ቁጥር ብርቅ ነህ ለኔ ዘዉድ ነህ አይቀልብኝም ምህረትህ አይቀልብኝም አይቀልብኝም ርህራሔህ አይቀልብኝም አይቀልብኝም ትግስትህ አይቀልብኝም አይቀልብኝም ጥበቃህ አይቀልብኝም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection