በማለዳ ሩጫ በዝቶ ድካም ዝለት ተንሰራፍቶ የጀመርነው መንገድ ቢርቅ ጀንበር ቀድማን ብትጠልቅ የ'ኛ ኹኔታ ፍጹም አንተን አይመዝንም ትልቅ ትልቅ ከማለት ከቶ አያግደንም አንተ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ነህ ከሁኔታ በላይ ትልቅ ነህ ከነገሮች በላይ ትልቅ ነህ ጌታ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ነህ ረሃብ ችግሩ ቢያይልም ሥጋችን ደክሞን ብንዝልም የመጣው ሕመም ቢከፋ መሄጃው መንገድ ቢጠፋ የምናልፍበት መንገድ በጥያቄ ቢ'ሞላ የጠላት ድምፅ ቢጮህም ሊስበን ወደኋላ በምንም ኹኔታ ውስጥ- እግዚአብሔር ላትተወን በእጆችህ እንደያዝከን- የነገርከን ቃል አለን። አንተ ትልቅ ኃያል ግሩም ነህ ከሁኔታ ሁሉ ታልፋለህ ከነገሮች በላይ ታላቅ ነህ ጌታ ሆይ ዘላለም ትልቅ ነህ፡፡ እግዚአብሔር ኾይ ትልቅነትህን ተረድተን እኛም አንጨርሰውም ከትናንትና ዛሬም እስከ ለዘለዓለም ትልቅነትህን አውቀን ከቶ አንጨርሰውም ባ'ለማት ሁሉ ፊደል ለቃላት በቀረፅነው አውቀናል ትልቅነትህን ችለን እንደማንገልጸው፡፡