Song Lyrics

ተነሥቷል

TENESTOAL

Feven Berhanu
Special Edition
መቃብሩ ባዶ ነው መቃብሩ እንደተናገረው ኢየሱስ ተነስቷል ህያው ነው ኢየሱስ ተነሥቷል ሞትን አሸንፏል አሀ ሀ በሞቱ ህይወትን አሀ ሀ በትንሣኤው መነሳትን አሀ ሀ በአብ ቀኝ መቀመጥን አሀ ሀ አገኘን ልጅነትን መውጊያው ተሰበረ ሲኦል ድል ተነሳ ሞትን አሸንፎ ኢየሱስ ተነሳ ዳግም ይመለሳል የወጉት ያዩታል እንደተስፋ ቃሉ ኢየሱስ ይመጣል/2 ኢየሱስ ተነሥቷል ሞትን አሸንፏል አሀ ሀ በሞቱ ህይወትን አሀ ሀ በትንሣኤው መነሳትን አሀ ሀ በአብ ቀኝ መቀመጥን አሀ ሀ አገኘን ልጅነትን እንደተረዳነው ከቅዱስ መጽሐፉ ዳግመኛ ሞተዋል ከሞት የተነሱ የእኛ ኢየሱስ ግን ላይሞት ተመልሶ አንድ ጊዜ ተነሥቷል ሲኦልን ድል ነስቶ/2 የለም የለም በመቃብር የለም የእኛ ጌታ ተቀምጧል በአርያም ቤዛ ሆኖልናል በመካከል ገብቶ ከሞት አስመለጠን በእኛ ፈንታ ሞቶ መቃብር መች ቻለ ይዞ ሊያስቀረው ተነሥቷል ኢየሱስ ዘላለም ህያው ነው/2 የለም የለም በመቃብር የለም የእኛ ጌታ ተቀምጧል በአርያም ተነሥቷል ኢየሱስ ተነሥቷል ተነሥቷል ሞትን አሸንፏል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection