ባንተ መንፈስ የተነካ ቦታ አይመርጥም የማምለኪያ ይዘምራል በዋለበት አያስችለው የሆንክለት ባንተ መንፈስ የተነካ ቦታ አይመርጥም የማምለኪያ ይዘምራል በሄደበት አያስችለው የሆንክለት በመንፈስህ ዝናብ የረሰረሰ ሰው ዛሬም አንተን ነገም አንተን አንተን ነው የሚለው(x2) እኔም አንተን አንተን አንተን አንተን ይልብኛል ልቤ(x2) እጅግ ልቀህ በሃሳቤ(x5) ደግሞ ልቀህ በሃሳቤ እጅግ ልቀህ በሃሳቤ መንፈስህ ከላይ ሲያገኘኝ ያሰረኝ ነገር ተፈታ ክብርህ ነፍሴን አበራት እንደ ጠዋት ፀሃይ ወገግታ ካንተጋ ውሎ እንዳደረ ፀዳልክ ፊቴ ላይ ቀርቶ ፍጥረት በሙሉ ተገርሟል (መልኬ ላይ መልክክን አይቶ)(x2) አልናግርም እንዲ ነው ብዬ ፍቅሩ ያረገኝን በምን አቅሜ ማውጣት አቅቶኝ አቅም ጨርሼ መግለፅ አልቻልኩም በምን ምላሴ አንተን በመውደድ ሸፍታ ነፍሴ በማያቋርጥ በምኞት አጥናፍ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) ከምናገረው ይላልቅ በኔ አፍ አንተን አንተን ይልብኛል ልቤ(x2) በመልካም ይሁን በክፉ ጊዜ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) በሰላም መንደር ወይ በትካዜ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) ከባህር ሰጥሞ በዝቅጠት አየርን እንደሚሻት ሰው ነፍሴ አንተኑ ትላለች በእውነት ፊትህ ምላለው ደመና በአየር ሲበተን ብርሃን ሲሄድ ጨልሞ ነፍሴ ግን እግርህ ስር አለች (በፍቅርህ አቅሟ ተዳክሞ)(x2) አልናግርም እንዲ ነው ብዬ ፍቅሩ ያረገኝን በምን አንደበቴ ማውጣት አቅቶኝ አቅም ጨርሼ መግለፅ አልቻልኩም በምን ምላሴ አንተን በመውደድ ሸፍታ ነፍሴ ኋላ ወደ ውሃ ምንጭ እንደምትጓጓ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) እንደምትናፍቅ መርካት ፈልጋ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) ክረምትም ይሁን በብሩህ ጊዜ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) በሰላም መንደር ወይ በትካዜ አንተን አንተን ይላል ልቤ(x2) ሁሌም አንተን አንተን አንተን አንተን ይልብኛል ልቤ(x2) እጅግ ልቀህ በሃሳቤ(x5) ደግሞ ልቀህ በሃሳቤ እጅግ ልቀህ በሃሳቤ