Song Lyrics

በፀጋ

Elora Gospel Singers
Special Edition
ያደረኩት የለም ስለመዳኔ (2) የከፈልኩት የለም ስለመዳኔ (2) እንዲሁ በነፃ ነው የዳንኩት እንዲሁ በፀጋነው የዳንኩት 1ጌታ ኢየሱስ ነው ለእኔ የሞተልኝ ከሀጢያት እርግማን ነጻ ያወጣኝ እራሱን ስለእኔ በርግጥ ሰውቶታል ነፍሴን ሊያድናት ደም ከፍሎላታል ወዶኝ ስላዳነኝ የለብኝ ኩነኔ እዳዬ ተከፍሎልናል ነጻ ነኝ እኔ ስራዬን መስቀል ላይ ሰርቶ ጨርሶታል በሞቱ ህይወቴን ከሞት ዋጅቷታል 2ግራ አልተጋባሁም አልተቅበዘበዝኩም ድነትን ፍለጋ ኢየዞርኩ ወጥቼ አልወረድኩም በማመኔ ብቻ በልጁ በኢየሱስ እኔን አድርጎኛል በአብ ቀኝ ከእርሱ ጋር እንድነግስ ቤቴን በሰማይ እርሱ ሰርቶልኛል መኖሪያዬን በላይ አዘጋጅቶልኛል አርፊያለው በእርሱ በነፍስ በስጋዬ የዘላለም ህይወት ሰጥቶኝ ኢየሱስ ጌታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection