በህይወት መዝገብ ፃፍከኝ በጽድቅህ ጻድቅ ሆንኩኝ ሰርቼ ሳይሆን በስራ ዳንኩኝ በፀጋ በሀጢያት የሞትኩኝ በህግ የተገደልኩ ሳለው ገና በአመፃ እያለው ጠላትህ እየሆንኩ ሳለው ገና ባንተ በልጁ ሞት ታረቀኝ አባትህ ቸር ጌታዬ በችንካርህ ብዕር ፃፍከኝ በመዝገብህ ቸር ጌታዬ የማያሳፍር ተስፋ ማይደበዝዝ የፅድቅ ብርሃን የማያሳዝን ተስፋ ማይቆጠር ልዩ ዘመን በዓይን ያልታየ ርዕስት ሀገር አለኝ በአባቴ ዘንድ መጥተ ትወስደኛለህ ጌታ ኢየሰስ የኔ መንገድ ጻፍከኝ በሕይወት መዝገብ ጻፍከኝ የኔ ስራ ሳይሆን ተቆጥሮልኝ ስራህ ድኛለው መዝኖ ከሀጢያቴ የሚጮሀው ደምህ ድኛለው ከህይወት መዝገብ ላይ መልአኩ አያጣኝም ድኛለው በፅድቅህ ተፅፌ ኩነኔ አይፍቀኝም ድኛለው አልጠፋም ከመዝገብህ በመንፈስህ ታትሜአለው ሊደመሰስ እንዳይችል ጌታ ባንተ አምኛለው በዚያ የህይወት መፅሀፍ ስሜ አለ በሰማያት በደምህ ወርሻለው ገብቻለው ወደ እረፍት ጻፍከኝ በሕይወት መዝገብ ጻፍከኝ ነውር የሌለበት እንድሆን በፊቱ የመረጠኝ የንጉስ ካህን አድርጎ የለየኝ ለዕርስቱ የመረጠኝ የእርሱን በጎነት ለዓለም እንድናገር የመረጠኝ ወደ ብርሃን ጠራኝ ከጨለማው መንደር አከበረኝ ከድቅድቁ ጨለማ ወደ ሚደንቅ ልዩ ብርሃን ጠራኸኝ ሙሽራዬ ወደ ክብርህ ልዩ ዙፋን በፀጋህ ነው የዳንኩት ከቶ አይደለም በኔ ስራ ዋስትናዬ ደምህ ነው እንዳልሰጋ እንዳልፈራ ለሀጢያት ፈቃድ አይደለም መዳኔና ነፃነቴ የእንደልብ ኑሮ እንዳይሆን የደም ዋጋ አለው ሕይወቴ ስጋዬ ደክሞ ብስት እንዳይገድለኝ ሀጢያት ደግሞ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለኝ የሚታይልኝ ለኔ ቀድሞ