Song Lyrics

ይኸው ልቤን

Carol Fekadu
Special Edition
ልቤን ላፈስልህ መጥቻለው ልቤን ላፈስልህ መጥቻለው ልቤን ልሰዋልህ ወድጃለው ልቤን ልሰዋልህ ወድጃለው ቁርባን እጣኔ ብዬ ማቀርበው ፊትህ ማፈሰው ሌላ አይደለም አንተ ምትወደው ይኸው ልቤን ነው ይኸው ልቤን ነው/3 ፊትህ ማፈሰው ይኸው ልቤን ነው/3 ላንተ ማፈሰው ሞርያም መጥቻለው ከመገኛህ ተራራ በልቤ ያዘልኩትን ላፍስሰው በየተራ አንተን አያስደስትህ ባመጣ የበግ አውራ ልቤ ይስሐቄ ነው ላንተ ያለኝን ልሠዋ ይኸው ልቤን ነው/3 ፊትህ ማፈሰው ይኸው ልቤን ነው/3 ላንተ ማፈሰው ሰማይ ዙፋንህ ሆኖ መቀመጫ ምድር ለእግሮችህ ሆና መርገጫ ግን የልቤን ዙፋን ወደድከው የኔ ጌታ ይኸው ልቤን ነው/3 ፊትህ ማፈሰው ይኸው ልቤን ነው/3 ላንተ ማፈሰው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection