Song Lyrics

አልተስማማም ሰማይ

Altesmamam Semay

Birhanemeskel W/medhin
Special Edition
እኔ ስል ለሞቴ ቀረኝ አንድ እርምጃ ውዴ ደረሰልኝ ሆነልኝ ማምለጫ አለቱን ሰንጥቆ ምንጭ አወጣልኝ ጠጥቼም ረካሁኝ ዳግም አቆመኝ አዝ:- አበቃ ያልኩት እኔ ነኝ አቃተኝ(አክትሟል )>> >> አይሆንም (ጨልሟል)>> >> (×2) እየሱስ ስለው ለኔ ነጋልኝ ውድዬ >> >> መጣልኝ (×2) ነጋልኝ አነጋልኝ መጣልኝ ውዴ ደረሰልኝ(×2) ነጋ ነጋ (Harmony) ተመካክሮ ነበር በኔ ጉዳይ ክፉ ቆራርጦ ሊጥለኝ በአሉባልታ ሰይፉ ሩጫዬን ሊገታ እንደቀላል አርጎ ጌታዬ አልነበረም በዚያ ህብረት ሸንጎ እሱ ከሌለበት በምክራቸው መሀል ልቤ ለአንድ አፍታ አረ እንዴት ይሰጋል ፍጥነቴን ሊያቆሙት ይሰበሰባሉ ባንድ መንገድ መተው በሰባት አቅጣጫ ይበታተናሉ የለበትም በምክራቸው መሀል >> >> ይቁም ይብቃው ሲባል >> >> ሲያሴሩ በኔ ላይ >> >> አልተስማማም ሰማይ (×2) አዝ:- አበቃ ያልኩት እኔ ነኝ አቃተኝ(አክትሟል )>> >> አይሆንም (ጨልሟል)>> >> (×2) እየሱስ ስለው ለኔ ነጋልኝ ውድዬ >> >> መጣልኝ (×2) ነጋልኝ አነጋልኝ መጣልኝ ውዴ ደረሰልኝ(×2) ነጋ ነጋ (Harmony) አበቃ ያልኩትን ታሪኬን ለውጦ አሻግሮ አቁሞኛል ነገሬን አስጊጦ ከፊቴ ያለውን ማዕበሉን ፀጥ አርጎ ዛሬም ይታደጋል ጌታ ጣልቃ ገብቶ አዝ:- አበቃ ያልኩት እኔ ነኝ አቃተኝ(አክትሟል )>> >> አይሆንም (ጨልሟል)>> >> (×2) እየሱስ ስለው ለኔ ነጋልኝ ውድዬ >> >> መጣልኝ (×2) ነጋልኝ አነጋልኝ መጣልኝ ውዴ ደረሰልኝ(×2) ነጋ ነጋ (Harmony) ሚድያምን ፈርቼ ተደብቄ ሳለው የሚያበረታ ቃል ከመላኩ ሰማው እጅጉን ቢበዛም ቢበረታ ሀይላቸው አምላኬ አስቧል በኔ ሊመታቸው ለካ እኔ ነኝ እንጂ አክትሟል ያልኩት በራሴ ሀሳብ ልክ ግምት ያኖርኩት ማንነቴን ሳይንቅ ፅኑ ሀያል ብሎኛል እኔ እሱን ታምኜ ምንስ ያስፈራኛል ምክራቸውን ስንፍና እያረገ እኔን ደግሞ በሀይል አስታጠቀ ተይዘዋል ባሴሩት ሴራቸው እንደ ብናኝ አርጎ በተናቸው(×2) አዝ:- አበቃ ያልኩት እኔ ነኝ አቃተኝ(አክትሟል )>> >> አይሆንም (ጨልሟል)>> >> (×2) እየሱስ ስለው ለኔ ነጋልኝ ውድዬ >> >> መጣልኝ (×2) ነጋልኝ አነጋልኝ መጣልኝ ውዴ ደረሰልኝ(×2) ነጋ ነጋ (Harmony
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection