Song Lyrics

ምህረትህ በዛ

Biniam Tilahun
Special Edition
ምህረትህ በዛ ጌታዬ ምህረትህ በዛ ምህረትህ በዛ ኢየሱስ ምህረትህ በዛ በዙሪያዬ ያለው ሲነጥፍ ደመና ከሰማይ ሲገፈፍ ልብ የተጣለበት ሲሰበር ተስፋ አካል ሳይለብስም ሲቀር አሁንስ ተስፋዬ ኸረ ማን ነው ሮጬ ማመልጠውስ ወዴት ነው /2* አንተ ግን በቃ አልክ ቃልህን ለኔ ላክ ተስፋዬን አደስከው ብርሃን ይሁን ብለህ ጨለማውን ገፈፍከው ፊትህን ልፈልግ ማልጄ ድምፅህን ለመስማት ጓጉቼ በእጆችህ መዳሰስ ናፍቄ መገኘትህን ሽቼ ከልቤ ማነክስባቸው ድካሞቼ ፊቴ ሲደቀኑ ፈ ር ቼ ልነሣ ስዳዳ ከፀሎቴ ምህረትህ እንደ ወንዝ ገባ ቤቴ አጠብከኝ በደምህ ተሰማኝ ያ ድምፅህ ፊትህም በራልኝ አንተ'ኮ ልጄ ነህ በርታ ጽና አልከኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection