Song Lyrics

እየጠበኩህ ነው

EYETEBEKUH NEW

Bereket Fekadu
Special Edition
ናና እየው ወዴት እንዳኖርኩት በልቤ ጓዳ ሸሽጌ ያኖርኩትን እኔና አንተ ብቻ በምናውቀው ጉዳይ መልስ እጠብቃለሁ ከሰማይ ኢየሱስ ላንተ ብቻ ባወጋሁ ጉዳይ መልስ እጠብቃለሁ ከሰማይ እየጠበቅሁ ነው ከትናንት ዛሬ አዳምጣለሁኝ ኮቴህን ከበሬ እጠብቅሃለሁ በመጠበቂያዬ አላሳንስህም በአንደበቴ ዝዬ ኮሽ ባለ ቁጥር አልደናበርም እየጠረጠርኩህ እምነቴን አልጥልም አንተ ላይ ነው አቅሜ የጩኸቴ ብርታት አቤቱ አቤቱ አቤት የምልበት ናና እየው ወዴት እንዳኖርኩት በልቤ ጓዳ ሸሽጌ ያኖርኩትን እኔና አንተ ብቻ በምናውቀው ጉዳይ መልስ እጠብቃለሁ ከሰማይ ኢየሱስ ላንተ ብቻ ባወጋሁ ጉዳይ መልስ እጠብቃለሁ ከሰማይ ደጅህን ብጠና እንደው ብመላለስ ፊትህን አትቀጭምም ከበር እንድመለስ ኮቴዬን ስትሰማ አይዝህም ዝለት የልቤን ተማጥኖ ቸል የምትልበት በተስፋ ለሚሹህ ለሚጠባበቁህ ታጠግባቸዋለህ ከመልካምነትህ ቢጠብቅ እስሩ ቢሸት መቃብሩ ባንተ ጊዜ ሲሆን ይሰማሀል ሁሉ አንተ ምታስበው ደግ ደጉን ብቻ መልካሙን ስለእኔ ብትነሳኝ ደሞ ብትከለክለኝ ብለህ ለጥቅሜ ብቻ ዝም አትበል አንድ ነገር በለኝ ትሁነነኝ ፍቃድህ ያልከው ይከተለኝ አይድጠኝም አፌን ለከንቱ ልሰለፍ ፀጋህ ይበቃኛል ባንተ ምክር ልረፍ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection